About US

Our Mission- ተልዕኳችን

Empower, educate, and integrate Black Canadians to live successful, productive lives in Canada

 

ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ የመጡ ወገኖቻችንን አቅም በማጎልበትና እና በማስተማር
ወደካናዳ ማኅበረሰብ የሚያደርጉትን የውኅደት ጉዞ ማገዝ።

OUR VISIOn- ራዕያችን

To support all Black Canadians to create healthy, inclusive, and positive lives in Canada. We serve as a bridge between Canadian and ethnic cultural/social systems. That bridge is designed to build stronger communities that will welcome and assist newcomers in a way that will allow for their seamless integration while increasing the likelihood of their becoming productive, successful, and proud citizens.

በካናዳ ኑሯቸውን ለማድረግ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ የመጡ ወገኖቻችን ጤናማ ፣
ሁሉን ዓቀፍ እና ቀና ኑሮን እንዲመሩ ማስተማር እና ማበረታታት። እንዲሁም በካናዳ
ባለውና ከመጣንበት ማኅበረሰብ በወረስነው ማኅበራዊ ስርዓቶች መካከል የመሸጋጋሪያ
ድልድይ ሆኖ ማገልገል። የድልድይነቱም ፋይዳ አዲስ መጪዎችንም ሆነ ሌሎች ትውልደ
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን የሚቀበልና የሚደግፍ ጠንካራ ማኅበረሰብ በመገንባት
የወገኖቻችንን የውኅደት ጉዞ በማቅለል ፍሬያማ፣ የተከናውነላቸው እና በማንነታቸው
የሚኮሩ ዜጎችን ማብቃት ይሆናል።

OUR VALUES- ዕሴቶቻችን

TEAMWORK- ተባብሮ መሥራት

We believe in each other. We have confidence and trust in the capabilities and objectives of our colleagues in our communities. We share knowledge and learn from each other. Collectively, we are focused on doing what is best for all families and youth.

እርስ በርሳችን እንተማመናለን። በማኅበረሰባችን ውስጥ ባሉ የሥራ ባልደረቦቻችን
ችሎታ እና ዓላማ ጽኑ እምነት አለን። እርስ በእርሳችን እውቀት እንከፋፈላለን፤
እንማማራለን። ለሁሉም ቤተሰቦች እና ወጣቶች የሚበጀውን ለማድረግ ትኩረት ሰጥተን
በጋራ እንሰራለን።

INTEGRITY - ታማኝነት

We do what we say we will do. Our relationships are based upon love, respect, and fairness in all our dealings and activities. Our actions demonstrate our integrity.

እናደርጋለን ብለን የተናገርነውን ቃላችንን ጠብቀን እንፈፅማለን። የትኛውንም ጉዳይ
ወይም ተግባር ስናከናውን የሚኖሩን ግንኙነቶች ሁሉ ደግሞ በፍቅር ፣ በመከባበር እና
በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረቱ ይሆናሉ። ድርጊቶቻችንም የአቋማችን ነፅብራቅ ናቸው። 

TRANSPARENCY- ግልፅነት

We will hold ourselves to a high standard of openness to maintain a culture of trust that directly translates into the way we approach effecting positive changes in the lives of the people in our community.

በበዙሪያችን ባሉ ወገኖቻችን ሕይወት አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማምጣት የሚያግዝ
የመተማመን ባህልን ለማጎልበት ፍፁም ግልፅነትን እናራምዳለን።

 

LOVE - መዋደድ

We believe that anything which is done with love can bring tremendous change to our communities. We approach all communities, families, and youth with love and respect, and work hard to establish strong and stable relationships within the families and youth for which we serve.

በፍቅር የሚደረግ ማንኛውም ተግባር በማኅበረሰባችን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ
እንደሚችል እናምናለን። ሁሉንም የማኅበረሰብ አካላትን፣ ቤተሰቦችን እንዲሁም
ወጣቶችን በፍቅር እና በአክብሮት እንቀርባለን፤ በቤተሰቦች እና በወጣቶች መካከልም
ጠንካራ እና የሰከነ መስተጋብር ለመፍጠር በትጋት እንሰራለን።

Why EXCEL FAMILY & YOUTH society
ኤክሴል የቤተሰብ እና የወጣቶች ማህበር ለምን አስፈለገ?

Excel Family & Youth Society has a great message to share with you! Most times people ask, "Why do we need Excel Family & Youth Society?" The video below shows a few of our volunteers and the Board of Directors discussing their experiences and stories.

According to Statistics Canada, the number of Ethiopian and Eritrean immigrants is growing by over 100% annually in Alberta and Canada. However, resources and an effective means of integrating these families into their new lives and country is lacking.

Excel Family & Youth Society (EFYS) was established to fill the gap between NGO’s and our growing, diverse communities. We bring together professionals, community associations, and faith-based organizations, in one medium, to work together towards building stronger, safer, and more productive communities.

EFYS endeavors to support all government and non-governmental agencies to effectively deliver their services to those in need, allowing for more sustainable Canadian, political, economic, and social systems.

ኤክሴል የቤተሰብ እና የወጣቶች ማኅበር (ኤክሴል) ለእርስዎ ሊያጋራዎ የሚወደው
ታላቅ መልዕክት አለ። ብዙ ጊዜ ሰዎች “ኤክሴል ለምን ያስፈልገናል?” ሲሉ ይጠይቃሉ።
ከዚህ ቀጥሎ ያለው ቪዲዮ ጥቂት ከኤክሴል ጋር የሚሰሩ በጎ ፈቃደኞች፣ እንዲሁም
የማህበሩ የቦርድ አባላት ልምዶቻቸውን እና ታሪኮቻቸውን ሲያጋሩ ያሳያል።

በስታቲስቲክስ ካናዳ የተለቀቀ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ኑሯቸውን በአልበርታ
እና በካናዳ ለማድረግ የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ቁጥር በያመቱ ከ100
ፐርሰንት በላይ እያደገ ነው። ሆኖም ግን እነዚህ ወገኖቻችን አዲሱን ኑሯቸውንና
አገራቸውን በአመርቂ ሁኔታ ለማላመድ የሚያግዙ መረጃዎችና ውጤታማ መንገዶች
በሚፈለገው መጠን አይገኙም።

ኤክሴል የቤተሰብ እና የወጣቶች ማኅበር፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በማደግ ላይ
ባለው ማኅበረሰባችን መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት የተቋቋመ ነው። የተለያዩ
ባለሙያዎችን፣ በማህበረሰባችን መካከል ያሉ ማህበራትን፣ እንዲሁም የዕምነት
ተቋማትን በማስተባበር ጠንካራ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀና የላቀ ውጤታማነት መገለጫው
የሆነ ማኅበረሰብን በጋራ ለመገንባት እንሰራለን።

ኤክሴል፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው
ወገኖቻችን አገልግሎቶቻቸውን በተሻለ መንገድ መስጠት እንዲችሉ በማገዝ በካናዳ
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና ማህበራዊ አካሄድ የበኩሉን ዘላቂ ድርሻ ለማበርከት
ይተጋል።